በሀገራችን የካሳቫ ምርት ኤክስፖርት እና አመራረት ዙሪያ በኢትዮጵያ እና በቻይና ኩባኒያ ተወካዮች መካከል ስምምነት ተደረገ፡፡
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 29 /2024 የካሳቫ ምርትን ወደ ቻይና ሀገር ለመላክ አስመልክቶ በሀገራቸን የተጀመረዉን ስራ የሚያግዝ ዉይይት ተደረገ፡፡በሚሲዮናችን በተደረገዉ ውይይት ላይ ክቡር አምባሳደር ተፈራ ደርበዉ በቻይና የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር በመሳተፍ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሀገራችን በካሳቫ ምርት ዙሪያ አቅም እንዳላት፣ በቀጣይ ምርቱን ወደ ቻይና ሀገር ለመላክ ለማስቻል በሁለቱም መንግስታት የሚመለከታቸው ተቋማት በኩል ግንኙነት እየተደረገ መሆኑን፣ካሳቫን ለማምረት እና ወደ ቻይና ሀገር ለመላክ የሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ ሚሲዮናችን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፇል ፡፡
በሀገራችን በኩል የካሳቫ ምርት አምራችና ላኪ ኩባኒያ Aleta Lands Coffee Plc እንዲሁም ኮንትራክተር እና አግሪጌተር OMO ADDDIS AGRICULTURE PLATFORM PLC-Ethiopia የቻይና ግዙፍ የካሳቫ ምርት ኢምፖርተር ኩባኒያ EC (NANJIN) INTERNATIONAL TRADE CO, LTD ባለቤቶች ጋር በካሳቫ ምርት ግዥ እና አመራረት ዙሪያ በስፋት ዉይይት የተደረገ ሲሆን ምርቱን በብዛትና በጥራት በማምረት እንዲሁም ወደ ቻይና ለመላክ የሚያስችል ስምምነት በቻይና የኢፌዲሪ ኤምባሲ በመገኘት ተፈራርሟል፡፡





